እንኳን ወደ መልህቅ ቤተሰብ  በደህና መጡ

ብቻዎን ሕይወትን መምራት አይጠበቅብዎትም!

መልህቅ መንደር ከግለሰቦች እና ቤተሰቦች ጋር በእያንዳንዱ የህይወት ደረጃ የሚራመድ ማህበረሰብ ነው።

 ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ህይወታቸውን በአሽናፊነት እንዲመሩ ለመርዳት በእውነት ላይ የተመሰረተ የምክር አገልግሎትን እንሰጣለን።

የምንሰጣቸው ፕሮግራሞች:

መልህቅ የሆነ ወላጅነት፡

ታስቦና ተጠንቶ ክህሎትንና በራስ መተማመንን ማዕከል ያደረገ የልጆች አስተዳደግ ድጋፍ መስጠት። 

መልህቅ የሆነ ጋብቻ፡

ጥንዶች ጠንካራ እና ዘላቂ ግንኙነት እንዲገነቡ መርዳት። 

መልህቅ የሆነ ወጣት፡

ታዳጊዎች በልበ ሙሉነት እና በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲያድጉ ማድረግ። 

መልህቅ የሆነ ሕይወት፡

ለላጤ ጎልማሶች ትርጉም ያለው ግንኙነት ለመገንባት፣ የግል ህይወት እድገትን ለመከታተል እና በእያንዳንዱ ወቅት ዓላማን ለማግኘትና ለመተግበር የሚያስችል ቦታ። 


ትንንሽ ልጆችን እያሳደጉም ሆነ፣ ለኑሮ አጋርነት ግንኙነቶችን እየፈጠሩ  ወይም ህይወትህን እንደ ግለሰብ ለመገምባት እየሞከሩ ከሆነ፣ መልህቅ መንደር አብረዎ ሊጓዝ ዝግጁ ሆኖ እዚህ አለልዎ። 


 መንደሩን ይቀላቀሉ ⟶